ቁጥር 2. ከንጽጽር ትርጉም መጽሐፍ የተወሰደ – የሃይማኖት ዕዉቀት ማስፋፊያ ማህበር (የሃ.ዕ.ማ.ማ)

ቁጥር 2. ከንጽጽር ትርጉም መጽሐፍ የተወሰደ

ቁጥር 2. ከንጽጽር ትርጉም መጽሐፍ የተወሰደ

ምዕራፍ አንድ

ምስጢረ ሥላሴ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውሃ ፈሳሽ ድንገተኛ የተገኘ አይደለም፡፡ በሥነ ፍጥረት ሥላሴ ‹‹ንግበር ሰብዓ በአርያነ ወበአምሳሊነ›› ብለዋል፡፡ ‹‹አምሳሊነ›› የተባለች ነፍስ ናት፡፡ ዘፍ. ም.1 ቁ.20-26፣ ም.16 ቁ.7-30 የሦስትነቱን አስረዳ፡፡ ዳዊትም ‹‹ዐቢይ እግዚአብሔር ወዐቢይ ኃይል ወአልቦ ኁልቁ ለጥበቢሁ›› ብሏል፡፡ ኢሳይያስም ም.6 ቁ.3 ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ›› ብሎ ሦስትነታቸውን ስብሃቲከ ብሎ አንድነታቸውን ተናገረ፡፡ መጽሐፈ ነገሥት ም.2 ቁ.2 ‹‹እስመ አልቦ ቅዱስ ዘእንበሌከ እግዚኦ››፡፡ ዳዊትም ‹‹ሐሠስኩ ገጽከ ገጸ ዚአከ አሃስስ እግዚኦ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ›› ብሏል፡፡ መዝ. 26 ቁ.8 ዳግመኛም ‹‹የማነ እግዚአብሔር አልአለተኒ›› ብሏል፡፡ መዝ. 118 ቁ.16 መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም በሉቃስ ወንጌል መንፈስ ቅዱስ ይመጽዕ ላዕሌኪ ወኃይለ ልዑል ይጼልለኪ ብሏል፡፡ ማቴ. ም.28 ቁ.35 ጌታም ወእንዘ ታጠምቅሙ በሉ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሏል፡፡ ማቴ. ም.28 ቁ.19 ይህንንም ሊቃውንት መሠረት በማድረግ ምሥጢረ ሥላሴን አብዝተው፣ አምልተው፣ አጉልተው ተናግረዋል፣ ተርጉመዋል፡፡ አምላክ ውእቱ አብ፣ አምላክ ውእቱ ወልድ፣ አምላክ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ኢይትበሃሉ ሰለሥተ አማልክተ አላ አሐዱ አምላክ ብሎ በሃይማኖተ አበው አትናቴዎስ ተናግሯል፡፡ ስለዚህ ሥላሴ ምንም በአካል፣ በስም በግብር ሦስት ቢሆኑ በባሕርይ፣ በመንግስት፣ በሥልጣን አንድ ስለሆኑ የአብ ሥም ሲጠራ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ስም አይለይበትም፡፡ እንደ ጊዜ ግብሩ አብና ወልድን አንስቶ  . . . . ሙሉዉን እዚህ በመጫን ያንብቡ፡

Share this

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *