ልዩ ልዩ የማኅበሩ ሪፖርት – የሃይማኖት ዕዉቀት ማስፋፊያ ማህበር (የሃ.ዕ.ማ.ማ)

ለአብያተ ክርስቲያናት የደረገውን ድጋፍ በተመለከተ

  • በማቴዎስ ወንጌል ም.16 ቁ.18 በዚህች ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሰራታለሁ ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት ሊቀ ትጉ. ባሕ. ገ/መስቀል ኃ/መስቀል ምዕመናንን በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር በማስተባበር አዳዲስ የተተከሉና ፈርሰው የታደሱ አብያተ ክርስቲያኖችን በማሰራት እስከአሁን በጠቅላላው ከ860 /ከስምንት መቶ ስልሳ/ በላይ በገጠርና በከተማ አሰርተው አስመርቀዋል፡፡ አሁንም በመሰራት ላይ የሚገኙ በርካታ ናቸው፡፡
  • በየወሩ በ3 ከምሕላ ጸሎት በኋላ ለአንድ ቤተክርስቲያን መዋጮ በማዋጣትና ቃል እንዲገቡ በማድረግ ለአብያተ ክርስቲያናቱና ለገዳማቱ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል፡፡
  • ምዕመናን የሚአዋጡትን ንዋየ ቅድሳት በአግባቡ በመሰብሰብ ከየአጥቢያ ቤተክርስቲያኑ የሚመጣውን ጥያቄ በመቀበል ጧፍ፣ እጣን፣ ሻማ፣ ጃንጥላ፣ ምንጣፍ አልባሳትና መጎናፀፊያ ወዘተ በየዓመቱ ከ6000 (ስድስት ሺህ) አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት በላይ በማደል የጸሎቱ ሥነ-ሥርዓት በአግባቡ እንዲካሄድ በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡
  • በቤተክርስቲያን ተተኪ አገልጋይ እንዲገኝ የአብነት መምህራንን በየገጠሩ በመቅጠርና ለተማሪዎች ድጋፍ በመስጠት እያስተማሩ የሚገኙ ሲሆን ለየአብያተ ክርስቲያኑና ገዳማት እንዲሁም ለአብነት ትምህርት ቤት የገቢ ምንጭ የሚሆኑ ድጋፎችና ማበረታቻዎችን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ለበርካታ አብያተ ክርስቲያናት ኮምፒውተር ከነፕሪንተሩ ገዝቶ በመስጠት በቤተክርስቲያን የተመደቡ ሠራተኞች ሥራቸውን አቀላጥፈው እንዲሰሩ እየረዳቸው ይገኛል፡፡