ነገረ መለኮት – የሃይማኖት ዕዉቀት ማስፋፊያ ማህበር (የሃ.ዕ.ማ.ማ)

ነገረ መለኮት

ናሁ ንጽሕፍ ነገረ እበያቲሁ ለእግዚአብሔር

ናሁ ንጽሕፍ ነገረ እበያቲሁ ለእግዚአበሔር

ለአንድ ጽሑፍ መግቢያ መቅድም አርዕስትና መደምደሚያ ሊኖረው ይገባል ፡፡ አንድ ጽሑፍ እነዚህ ነገሮች ከሌሉት አቅጣጫ ጠቋሚ መሳሪያ እንደሌለው መርከብ ወይም ኮምፓስ እንደሌለው አውሮፕላን ነው፡፡ያ የት እንደሚሄድ እንደማያውቅ ሁሉ አንባቢውም የጽሁፉን ዋና ሃሳብና አላማ በቀላሉ ለመረዳት ይቸገራል፡፡ መግቢያ ማለት የጽሑፉ ዋና በር ማለት ነው፡፡ በር ካልተከፈተ ወደ ሰው ቤት መግባት እንደመይቻል ሁሉ መግቢያ የሌለው ጽሑፍም ለአንባቢው የተዘጋ በር ነው፡፡ መቅድም ማለት ከጽሑፉ አስቀድሞ የሚገኝ ወሣኝና ፍሬ ቃል ነው፡፡ መቅድሙን ልብ ብለን ካስተዋልነው  የአርዕስቱ የመደምደሚያውና የመግቢያው የጽሁፉ ቁልፍ ሚስጢር ነው ፡፡ አርዕስት ማለት በጽሁፉ ውስጥ ስንት ዋና ዋና ሀሳብ ቃላት ዓረፍተ ነገርና ሐረግ እንዳለ የሚወስንና የሚያሳውቅ ክፍል  ማለት ነው ፡፡ መደምደሚያ  ማለት የጽሑፉ መቋጫ መጨረሻ ማጠቃለያ ማለት ነው፡፡ ወደ ዋናው ሃሳባችን እንግባ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ነገረ መለኮት ማለት የእግዚአብሔር ስም፤ክብር፤ከሐሊነት፤ማንነት መንግስት፤ እንዲሁም የፍጡራንን ማንነትና የመፈጠራቸውን አላማና ምክንያት የሚያስረዳ ፤ የመጀመሪያውና የመጨረሻው የዕውቀት መሠረት ነው፡፡ ይህን ማለታችን ነገረ መለኮት የማይነካውና የማይዳስሰው የዕውቀት አይነት ስሌለ ነው፡፡  ነገረ መለኮትን አለማወቅ እራስን እንዳለማወቅ ይቆጠራል፡፡ እስከዚህ ከሁለት የተከፈለ አርዕስት ነው፡፡ ለሁለቱም እንደ ቅደም ተከተል ያመጣል፡፡ ከስሙ ትርጓሜ ይጀምራል፡፡ እግዚአብሔር ማለት አብ ፤ወልድ ፤መንፈስ ቅዱስ ዘለዓለም ሥላሴ አንድ አምላክ ማለት ነው፡፡ ለቀዳማዊነቱ መጀምሪያ ለደሃራዊነቱ መጨረሻ ለማዕከላዊነቱ መወሰኛ የሌለው እፁብ እፁብ ብቻ እየተባለ መመስገን የሚገባው ዘለዓለማዊ አምላክ ነው መንክርሰ እግዚአብሔር በአርያሙ እንዲል መዝ.92፡4የስሙ ትርጓሜ ይህ ሲሆን ስለማንነቱ ወደፊት ያመጣል፡፡ መለኮት የሚለው ቃል፡፡ የሰው ሕሊና የመላዕክት አእምሮ ተመራምሮ የማይችልበት ረቂቅ የሆነ የእግዚአብሔር ማንነት ነው ሊደረስበትም የማይቻል የእገዚአብሔር ታላቅነት ነው፡፡ ስለዚህ በጥበብና በማስተዋል እናንብብ 

 

 

ንግባዕኬ ኃበ ጥንተ ነገር

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ ቅዳሴ ማርያም ቁጥር 79

 እግዚአብሔር ማነው? ሥራውስ ምንድነው? ይህንን ዓለም እንዴት ፈጠረው? ዓለምን ከመፍጠሩ በፊት እንዴት ባለሁኔታ ይኖር ነበር? የሚል ጥያቄ በአእምሯችን  ስለሚመላለስብን ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ማንነትና ሥራ ለመግለጽና ለማብራራት ቅዱሳት መጻህፍትን ዋቢ በማድረግ የተቻለንን ያህል እንሞክራለን ከስሙ ትርጓሜ ስንነሳ እግዚኔ ማለት፡ ገዥ፡ ጌታ፡ ሲሆን ፡ ገዝዐ፡ ገዛ፡ ከሚለው፡ የግእዝ፡ ቃል፡ የተገኘ ፡ነው፡፡ሲናበብ እግዚአብሔር የሚል ዐረፍተ ነገር ይሰጣል የስሙ ትርጓሜ የሚታየውን እና የማይታየውን ዓለም የማይዳሰሰውን ረቂቁን የሚዳሰሰውን ግዙፉን ፍጥረት ፈጥሮ የሚገዛ የባሕርይ አምላክ ማለት ነው፡፡ በነገራችን ላይ እግዚአብሔር በሚለው ስም መጠራት የጀመረው ይህንን ዓለም ከፈጠረበት ዕለት ጀምሮ ነው፡፡ስንል እግዚአብሔር በፊት የለም ማለት አይደለም፡፡ይልቁንስ አለምን ከመፍጠሩ አስቀድሞ በአንድነት፣ በሶስትነት፣ በመንግስት ፣በስልጣን በአገዛዝ ፣በመለኮት፣ በከሐሊነት ጸንቶ እንዴት ሲመሰገን ሲቀደስና ሲወደስ እንደነበረ ከማይመረመረው ቀዳማዊ ረቂቅ ባሕርዩ ለመግለጽ ስለፈለግን ነው እንጂ፡፡ እግዚአብሔር አለምን ከመፍጠሩ በፊት በባሕርዩ ንጉሥ ነው፡፡ የተወደዳችሁ ወድ የእግዚአብሔር ልጆች ለፍጥረታት ሁሉ የሚሆን ለቅምሻ ያክል እነሆ መጽሔታችን መልካም የንባብ ጌዜ ይሁንልን ወድ  የመጽሔታችን አንባቢያን በሙሉ በተረጋጋና በሰከነ መንፈስ ሆነን በዚህ ጽሑፍ የመለኮትን ምንነት እንወቅ እንላለን ከመጽሔት ዝገጅት ክፍል፡፡

       እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም