ዓላማ – የሃይማኖት ዕዉቀት ማስፋፊያ ማህበር (የሃ.ዕ.ማ.ማ)

የማኅበሩ ዋና ዋና ዓላማዎች

የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማኅበር ዋና ዋና ዓላማዎች፡-

  • የክርስትና ሀይማኖትን በማስፋፋት የመጽሀፍ ቅዱስ ትምህርት በማስተማር የሀይማኖት ዕውቀትን ማስፋፋት
  • የሀይማኖትን በሚፈቀደው ደነብና ስርዓት መሰረት ለህብረተአቡ በልዩ ልዩ ተቅዋማት የሀይማኖት ትምህርት በመስጠት የመዕመናኑን እውቀት ማጎልበት
  • ለአረጋዊያን ለወጣቶችና ለሕጻናት በፕሮግራም መጽሐፍ ቅዱስ በማስተማር ምዕመናኑ የመዝሙር የድርማና የስነ-ጽሑፍ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ
  • የሀይማኖትወ መቀራረብ እዲኖር የመወያያ መድረኮችን በማዘጋጀት ማወያየት
  • በአካባቢ ዕድር፣ በልቅሶና በሠርግ ላይ በመገኘት የማጽናኛ ትምህርት በመስጠት ሰዎችን ለንስሐ እንዲበቁ ማድረግ፣
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርስ በመስጠት የሥነ-ምግባር ዕውቀትን እንዲያገኙ የማድረግ የገጠር ቤተክርስቲያን እና ገዳማትን መርዳት፤
  • የአልጋ ቁራኛ ሆነው የቀሩትን አረጋውያንና እናት አባት የሞተባቸውን ሕፃናት በድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎት መርዳት ናቸው፡፡

የማኅበሩ ሕጋዊ ዕውቅና ማግኘትን በተመለከተ 

የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማኅበር ህጋዊ ዕውቅና ያገኘው ከፌዴራል የአርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖት ድርጅቶችና ማኅበራት ምዝገባ ዳይሬክቶሬት ሲሆን ሁለተኛ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ስር ሆኖ እንዲንቀሳቀስ የተፈቀደለት ሲሆን በእነዚህ የመንግስትና የሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ህጋዊ ዕውቅና አግኝቶ የሚንቀሳቀስ ማህበር ነው፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ማቴ. ም.10 ቁ.1

የማህበሩን አደረጃጀት በተመለከተ

የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማኅበር አደረጃጀቱ፡-

ሀ. የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ያለውና የሥራ አስፈፃሚ አፈጉባኤ ያለው ሲሆን በዓመት ሁለት ጊዜ ይሰበሰባል፤ ሥራዎችን ይገመግማል፣ ውሳኔዎችንም ያስተላልፋል፡፡

ለ. የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ቁጥራቸው አምስት ሆኖ በየአምስት ዓመቱ አንድ ጊዜ በጠቅላላ ጉባኤው ምርጫ በነፃ አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡

ሐ. የበጎ ፈቃደኞች አገልግሎት በልዩ ልዩ የኮሚቴ አደረጃጀት ውስጥ በመግባት የሥራ አመራር ቦርዱን በማማከር ለሠራተኞች ስልጠና በመስጠት ማገልገል ይቻላል፡፡ ዝርዝሩም፡-

  1. የቅስቀሳና አስተባባሪ ኮሚቴ፣
  2. የማስታወቂያና የሚዲያ ሥርጭት አገልግሎት ኮሚቴ፤
  3. የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ድጋፍ ሰጪና አማካሪ ኮሚቴ፤
  4. የቤት ለቤት ድጋፍና እንክብካቤ ኮሚቴ፤
  5. የመንፈሳዊ ጉዞ አመራር ኮሚቴ፤
  6. የሥነ-ጽሑፍና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ኮሚቴ፤
  7. የመንፈሳዊ ጉባኤ አስተናጋጅ ኮሚቴ፤
  8. የሥልጠናና የትምህርት አገልግሎት ኮሚቴ፤
  9. የፕሮጀክት ጥናት ኮሚቴ፤
  10. የገቢ አሰባሳቢ አመራር ኮሚቴ፤
  11. የውስጥ ቁጥጥርና ክትትል ኮሚቴ፤
  12. የገጠር አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ጥናትና ክትትል ኮሚቴ፤
  13. የማኅበሩን አባላት አደራጅና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማስፋፊያ ቅስቀሳ ኮሚቴ፤
  14. የበአል ዝግጅት አመራር ሰጪ ኮሚቴ፤
  15. መቶ ሃያ የክርስቶስ ቤተሰቦች የአርድእት ኮሚቴ

በጠቅላላው ከ200 /ሁለት መቶ/ ሰዎች በላይ በኮሚቴነት ተመርጠውና ተሰይመው በፍቅርና በአንድነት መንፈሳዊ አገልግሎቱን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ለቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው፡፡ እናንተም መጥታችሁ በፈለጋችሁት ኮሚቴ ውስጥ ገብታችሁ ለማገልገል የምትችሉ መሆኑን ስንገልጽላችሁ በደስታ ነው፡፡

መ. የማኅበሩ ሠራተኞች እስከአሁን ቁጥራቸው 27 የደረሰ ሲሆን በየወሩ ደመወዛቸውን በመክፈል በየተመደቡበት የስራ ዘርፍ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

ሠ. በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑት ክርስቲያኖች የማኅበሩ አባል በመሆን በጉልበታቸው፣ በዕውቀታቸው፣ በገንዘባቸው ለማገልገል የበጎ ፈቃደኛ የሆኑና በራሳቸው ፍላጎትና ፈቃድ ተመዝግበው ለቋሚ አባል ከ5 ብር ጀምሮ፣ ለክብር አባል ከ100 ብር ጀምሮ፣ ለዕድሜ ልክ አባል 10000.00 ብር በመክፈል በርካታ የማኅበሩ አባላት አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ በየትኛውም ዓለም ላይ ሆነው የማኅበሩ አባል መሆን የሚችሉ ሲሆን በየወሩ በዚህ የባንክ ሂሳብ ቁጥር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀጨኔ ቅርንጫፍ 1000024970691 /ብሔራዊ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01704-17922000 የአባልነት ክፍያችሁን መላክ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የአባልነት መስፈርቱ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ መሆን ብቻ በቂ ነው፡፡