የስብከት አገልግሎት – የሃይማኖት ዕዉቀት ማስፋፊያ ማህበር (የሃ.ዕ.ማ.ማ)

የስብከተ ወንጌል አገልግሎት

1ኛ. በሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማኅበር የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በሳምንት አምስት ቀን ረቡዕ ሀሙስ አርብ ቅዳሜና እሁድ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ የመሀረነአብ ጸሎት ይጀመርና 11፡30 ሰዓት ይመናቀቃል፡፡ ከዚያም የመሸጋገሪያ መዝሙር ተዘምሮ የእለቱ አባኪ ደግሞ ወንጌል ለ40 ደቂቃ አስረምሮ በአንድ ሰዓት ጉባኤው በጸሎት ይዘጋል፡፡ ሎላው ደግሞ በየሳምንቱ እሁድ እሁድ ‹‹መቅላላ ዕውቀት›› በሚል ርዕስ ብቁ በሆኑ መምህራን ትምህርት ይሰጣል፡፡ እንዲሁም በመጽሐፍ በቨሲዲ በበራሪ ወረቀት በፌስቡክ በዋትስአፕና በዩትዩብ ለዓለም አቀፍ ትምህርት ይሰጣል፡፡

 

2ኛ. ጠዋት ጠዋት ከ2፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ለጠበል ተጠማቂዎች ተአምረ ማርያም ከተነበበ በኋላ የስብከት አገልግሎት ይሰጣል፤

3ኛ. በየወሩ በቋሚነት ከ1 እስከ 7 ቀን ድረስ ለ7 ቀን ዳዊት ይደገማል፤ ጸሎተ ምሕላ ይደረሳል፤ የስብከት አገልግሎት ለካህናትና ለምዕመናን ይሰጣል፤

4ኛ. በየወሩ በ3፣ በ7፣ በ12፣ በ16፣ በ21፣ በ23 እና በ29 በዚሁ በምዕራፈ ቅዱሳን የሰገነት ኪዳነምሕረት ቤተ ጸሎት ጧፍ ይበራል፣ ጸበል ጸዲቅ ይቀመሳል፣ በተጋ ባዥ ዘማርያንና ሰባክያነ ወንጌል ሞቅ ደመቅ ያለ ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ ይካሄዳል፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡

5ኛ. በወር 2 ጊዜ ከዓርብ እስከ እሁድ ለሦስት ቀን በየሀገረ ስብከቶች ግብዣ በገጠር ቤተክርስቲያን እና ገዳማት እስፖንሰር በመሆን ሙሉ ትራንስፖርት መስጠት የሚችል መኪና በመመደብ ሰባክያነ ወንጌልና ዘማርያን እንዲሁም የክራር ተጫዋች ሙሉ አበላቸውን በመቻል ለምዕመናን ለሦስት ቀን መንፈሳዊ ጉባኤ አካሂደን እንመለሳለን፡፡ ማቴ. ም.5 ቁ.1-12

6ኛ. በ7 እና በ21 በመንፈሳዊ ጉባኤያችን ላይ ምዕመናን እግዚአብሔር ስላደረገላቸው መልካም ነገር ምስክርነት በመስጠት ስዕለታቸውን ያገባሉ፡፡ ይህም ምስክርነት በየወሩ ሁለት ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን በእነዚሁ ዕለታት ጥያቄና መልስ ይካሄዳል፡፡

7ኛ. በየሳምንቱ ቅዳሜና እሁድ በማኅበሩ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 8፡30 ለሕፃናት፤ ከ8፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት ለወጣቶች በሰንበት ት/ቤት ውስጥ ለሚማሩ ህፃናትና ወጣቶች የሥነ-ምግባር፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም፣ የመዝሙር ጥናትና የስነ-ጽሑፍ ትምህርት በተመደቡላቸው መምህራን ትምህርትና ምክር ይሰጣቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡