ሚየዚያ 1/ 08/ 2010 ዓ. ም የነዳያን ግብዣ ተደረገ – የሃይማኖት ዕዉቀት ማስፋፊያ ማህበር (የሃ.ዕ.ማ.ማ)

ሚየዚያ 1/ 08/ 2010 ዓ. ም የነዳያን ግብዣ ተደረገ

June 25, 2018
አዳዲስ

ሚየዚያ 1/ 08/ 2010 ዓ. ም የነዳያን ግብዣ ተደረገ፡፡ ልክ ክርሰቶስ በዮሐ 5፡1-9 ረዳት ለሌላቸው ያሳየውን ፍቅር
ለማስታወስና ለወንድሞቻችን ከመድኃኒታችንኢየሱስ ክርስቶስ የተማርነውን ፍቅር በመግለጽና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስለእነሱም ጭምር እንደሞተላቸው በመንገር በመንፈሳዊ ምግብ ቃለ እግዚአብሔርና በስጋዊ ምግብ ተስተናግደዋል፡፡ ስለዚህ ይህ የነዳያን ግብዣ በአመት አራት ጊዜ ይካሄዳል ከፕሮግራሞች መካካል በአንደኛ ደረጃ ወንጌልይሰበካል በመንፈስ የተራበውን ሰው መንፈሳዊ ምግብ መግቦ ለስጋ ደገሞ የሚሆን ምግብን ተስተናግደዋል፡፡ በቅድሚያ መንፈሳዊ ምግብ ስለሆነ የሚያስፈልግ ትመህረተ ወንጌልተሰጥቷል፡፡ ከተሰጠ በኋላ ከዚያ በመቀጠል የማጠቃለያ ጸሎት ይደረግና ሁሉም ባሉበት ቁጭ እንዳሉ የምግብ መስተንግዶ ይጀመራል፡፡ የበሉት ሲወጡ ደግሞ ያልበሉት ይገባሉ ልክ እንደ መጀመሪያው መርሃ ግብር በመጀመሪያ ወንጌል ይሰበካል ከዚያ በመቀጠል ወደ መስተንግዶ ይገባል፡፡ የሐይማኖት ዕወቀት ማስፈሰፊያ ማህበር አንዱዋናአላማው ልክ ክርስቶስ ለሰው እንደኖረ ሁሉ የመህበሩ አላማም ለሰው መኖር ነው፡፡

Share this

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *