የማህበሩ አመሰራረት

የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማኅበር ህጋዊ ዕውቅና ያገኘው ከፌዴራል የአርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖት ድርጅቶችና ማኅበራት ምዝገባ ዳይሬክቶሬት ሲሆን ሁለተኛ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ስር ሆኖ እንዲንቀሳቀስ የተፈቀደለት ሲሆን በእነዚህ የመንግስትና የሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ህጋዊ ዕውቅና አግኝቶ የሚንቀሳቀስ ማህበር ነው፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ማቴ. ም.10 ቁ.1

በጠቅላላው ከ200 /ሁለት መቶ/ ሰዎች በላይ በኮሚቴነት ተመርጠውና ተሰይመው በፍቅርና በአንድነት መንፈሳዊ አገልግሎቱን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ለቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው፡፡ እናንተም መጥታችሁ በፈለጋችሁት ኮሚቴ ውስጥ ገብታችሁ ለማገልገል የምትችሉ መሆኑን ስንገልጽላችሁ በደስታ ነው፡፡

መልካም ስራ ለመስራት አትታክቱ

መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአትበደጅ ታደባለች ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው አንተ ግን በእርስዋ ንገስባት

ኦሪ.ዘፍ ም 3 ቁ 6

በዓለ ጥምቀት

            ሸክላ ሰውነታችን ድኅረ ተሰብረ አጽንዖ ለሰብእናነ ልሕኵት፣ ለብሐዊ ክርስቶስ በማየ ሐዲስ ጥምቀት። ትርጉም፦ ሸክላ ሰውነታችን ከተሰበረ በኋላ ጥበበኛ/ሸክላ ሠሪ ክርስቶስ በአዲስ ውኃ ጥምቀት መልሶ አጸናው (መልሶ አደሰው)። ይህ የቀደምት አባቶቻችን ቅኔ የሚያስረዳን ነገር አለው። እንደሚታወቀው ሸክላ ሠሪ ሸክላዋን ከሠራች በኋላ ነቅ ብታገኝበት ወይም ቢሠበርባት ታፈርሰውና እንደገና በውኃ አርሳ መልሳ አዲስ አድርጋ ትሠራዋለች። ሸክላውም ከፊተኛው ይልቅ የጸና እና ቶሎ የማይሰበር ይሆናል። በዚህ አንፃር ባለቅኔው የገለጡት የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጣሱና አትብላ የተባለውን ዕፀ በለስ በመብላቱ ከእግዚአብሔር ተለየ ፣ ጸጋውን ተገፈፈ፣ ልጅነቱን አስወሰደ በዚህም ምክንያት በሞተ ሥጋ ላይ ሞተ ነፍስ በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነም ተፈረደበት። ስለሆነም ሰውታችን እንደሸክላው በኃጢአት ፈረሰ ...
Read More

ግንቡ ፈረሰ

ጥር ፯ ቀን የሥላሴ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በደመቀ መልኩ በማኅሌት ፣ በቅዳሴ ፣ በመዝሙር ፣ በምስጋና እና ወንጌልን ለምዕመናን በማስተማር ይከበራል። አሁን የሥላሴ በዓል ይከበራል ስንል ሥላሴ በአንድ ቀን ብቻ ታስበው ይቀራሉ ማለት አይደለም ምንም ሁልጊዜ ተአምር ሠሪ ቢሆኑም በትዕቢተኞች ላይ ልዩ ተአምር የሠሩበትን ቀን ለሰው ለማሳወቅ ነው እንጂ። ጥንተ ነገሩ እንዲህ ነው ከጥፋት ውኃ በኋላ የኖኅ ልጅ ካም ኩሽን ወለደው ፣ ኩሽም ናምሩድን ወለደው። ናምሩድም በምድር ላይ ኃያል እና አዳኝ ነበረ። ናምሩድን ጨምሮ ሌሎችም የኖኅ የልጅ ልጆች ሁሉ በአንድነት ይኖሩ ነበር። ከምሥራቅ ተነሥተው ወደምዕራብ ሀገር ሲሄዱ በሰናዖር ምድር ሰፊ ሜዳ አገኙና በዚያ መኖር ጀመሩ። ከዚያ በኋላ፦ "እርስ ...
Read More

ምኩራብ

                                   የዓብይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት ምኩራብ ማለት የአይሁድ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት እንዲሁም ታላቅ አዳራሽ ማለት ሲሆን ለአምልኮና ለትህምህርት መማሪያ ይገለገሉበት ነበር፡፡ ምኩራብ በአለቆች ይመራ ነበር፡፡ (ማር 5÷22፣ ዮሐ 3÷14-15,18÷8) በእየሳምንቱ ሕዝቡ ሁሉ በምኩራብ ይሰበሰቡ ነበር (ሉቃስ 4÷16፣ የሐ.ሥ 15÷21) ወንዶችና ሴቶች ለእየብቻቸው ይፀልዩና ይቆሙ እንዲሁም ይቀመጡ ነበር፡፡ ታዲያ ይህ ሳምንት ለምን ምኩራብ ተባለ? ሲባል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምዋለ ስብከቱ ለማስተማር ወደ ምኩራብ ገብቶ ነበርና ለዚያ መታሰቢያ እንዲሆን ምኩራብ ተብሏል (ማቴ 4÷23፣ ማር 1÷21፣ ሉቃ 4÷15) ወደ ዚህም ምኩራብ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ቀን ሊያስተምር ሲገባ አይሁድ ቤተ ጸሎቱን እንደ ስያሜው ሳይሆን መሸጫና መለዋወጫ፣ መገበያያ አድርገውት ስለአገኛቸው ‹‹ቤቴ የጸሎት ቤት ...
Read More

ቅድስት

                             የዓቢይ ጾም ሁለተኛ ሣምንት ቅድስት ይባላል፡፡ ቅድስት ማለት የተቀደሰች፣ የተባረከች፣ ንጽሕት፣ ልዩ የተመሰገነች ማለት ነው፡፡ ቅድስት የተባለበት ምክንያት ‹‹ጾምን ቀድሱ ጉባኤውንም አውጁ ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ (ኢዩ 1÷14) ብሎ በነቢዩ በኢዩኤል አድሮ የተናገረ ቅዱስ እግዚአብሔር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾማት ጾም ስለሆነች ቅድስት ትባላለች፡፡ እንዲሁም የዲያብሎስን ፈተና ድል ለመንሳት በቅድስት ከተማ በኢየሩሳሌም በሰሎሞን ቤተ መቅደስ ጫፍ የቆመባት ዕለት ሰው ጾምን ጾሞ እንደፈጣሪው ፈተናን ድል ነስቶ ቅድስናንና ክብርን ያገኛል፡፡ ለምን ብየ ቅድስቴን ጾምኳት እንዲሉ መጾም ቅድስናን ለማግኘት ነውና፡፡   ታዲያ ይህቺ የጌታችን ጾም ቅድስት ተብላ መጠራቷ የሚጾማትን ስለምትቀድስ ነው፡፡ ...
Read More
Loading...

ትምህርተ ሃይማኖት

ማስታወቂያ

ማህበሩን ማገዝ ለምትፈልጉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሂሳብቁጥር:- 0170417922000

ሚድያ


ውድ የፌስቡክ “ጓደኞቻችን” ቁጥር 5 ሺህ በመሙላቱ አዲስ ሰዎችን መጨመር አንችልም። ስለዚህ አዳዲሶችም ሆናችሁ የቀድሞ የፌስቡክ ጓደኞቻችን ከዚህ በታች ያለውን “Like” የሚለውን ቃል በመጫን በዚያ እንድትከታተሉን በትህትና እንጠይቃለን።

መርሀ ግብር

በማህበሩ የተዘጋጁ መፅሐፎች

የማህበሩ አባል ለመሆን እዚህ ይመዘገቡ!

ቪድዬ ቻት